Amhaic

በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ቪድዮ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ – (Click here to watch the Video)

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት የአዲስ አበባን አስተዳደር ለማስፋት ያዘጋጀው አዲሱ የመሬት ካርታ ወይም ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንደሚደረግ የመንግስት ባለስልጣናት የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን እየቀጠሉ ሲሆን፣ በአምቦ፣ ኤሉባቦር፣ በምእራብ ወለጋና በሌሎችም የተካሄዱት ተቃውሞዎች ወደ ሃሮማያ (አለማያ)ዩኒቨርስቲ ተዛምቶ፣ በተማሪዎችና በፖሊስ መካከል በተነሳው ግጭት፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል።ESAT News in Amharic, Oromo students protest

ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን በሰላም በማሰማት ላይ እያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ዩኒቨርስቲው ግቢ በመግባት ድብደባ በመጀመራቸው ከ30 ያላነሱ ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ህክምና መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮች ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ ተማሪዎችን ቁጥር በትክክል ለማወቅ ባንችልም፣ የተወሱ ተማሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። አንድ የፌደራል ፖሊስም በድንጋይ መመታቱንና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ የተወሰኑ ተማሪዎች ግቢው በመልቀቅ ወደ ሃረርና ድሬዳዋ ሄደዋል።

በሌላ በኩል ዬዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ከዩኒቨርስቲው አመራሮች፣ ከኦህዴድ አባላትና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ሲወጡ መወሰድ ስለሚኖርበት እርምጃ ግልጽ የሆነ መመሪያና እቅድ ባለመተላለፉ ፣ መቸገራቸውን ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። የስብሰባው ተሳታፊ ነበሩ የኢሳት ምንጮች በድብቅ ቀርጸው በላኩት ድምጽ፣ የተለያዩ ተወካዮች፣ ፕ/ሩ ተቃውሞ እንደሚነሳ እያወቁ መረጃ አስቀድመው ባለማሳወቃቸው ወቀሳ አቅርበዋል። ይሁን እንጅ ፕ/ር ጨመዳ፣ ተቃውሞ መነሳቱን የሰሙት እሁድ ሌሊት መብራት ጠፍቶ በነበረበት ወቅት መሆኑን፣ ዛሬ ሁኔታው መባባሱን ገልጸዋል።

ተቃውሞዎች ሲነሱ ፣ የፖለቲካ ስራ በመስራት እናሳምናለን ቢባልም፣ ተማሪዎች አናምንም ካሉ ስለሚወሰደው ቀጣይ እርምጃ ግልጽ የሆነ እቅድ ባለመኖሩ፣ ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል መንግስት የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ወደ ተግባር ከመቀየር ወደ ሁዋላ እንደማይል አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ተናግረዋል።

ኤሊኖ ወይስ አውሮቦሮሶች? (ነጋ አባተ ከእስራኤል

ነጋ አባተ ከእስራኤል

ሰሞኑን ድኅረ- ገፆቻችንን ያጥለቀለቀው ዓቢይ ጉዳይ “ርሃብ” በሚባል ጨካኝ ምጣድ ላይ ተዘርግፈው እየተቆሉ ላሉ ወገኖቻችን የእንድረስ ጩኽትን የሚያስተጋባ የፌስ ቡክ “የክፉ ቀን” ዘመቻ ይመስለኛል። ምንም እንኳን ዕንቅስቃሴአችን ከጩኽት መዝለሉን እርግጠኛ ባልሆንም እኔም በጓደኞቼ አማካኝነት ተሳታፊ ሆኛለሁ። ቆይ ግን ጎበዝ! ቆም እንበል በእውነት ክፉ ቀን ወይስ ክፉ ጠላት? ኤሊኖ ወይስ አውሮቦሮሶች?። “አህያውን ሲፈሩ መደላድሉን” እንዳይሆን ብየ ነው።El no drought in ethiopia

የፌስ ቡኩን ዘመቻ የከፈቱት ወገኖቼ በንጉስ በአጤ ምኒልክ ዘመነ- መንግስት ከ1880-1884 የተከሰተውንና ወገናችንን በመሮ ጥርሱ አድቅቆ በትውልድ መካከል የማይደብስ ጠባሳ ጥሎብን ያለፈውን እነኝያ “ክፉ ቀን” በመባል የሚታወቁትን ድርብርብ አሰቃቂና ማቅ-ለበስ ዐመታት ስያሜ በመውሰድ የተጀመረ ዕንቅስቃሴ ይመስለኛል። አዎ! ከባድ ዓመታት ነበሩ ክፉ ቀን የሚል መጠሪያ ይዘውም በታሪክ መዝገብ ከነግሳንግሳቸው ሰፍረዋል። ሌላው ሳይቀር ወራሪው የጣሊያን ጦርም ስለርሃቡ መረጃው ስለነበረው ይህንን ክፉ አጋጣሚ ተጠቅሞበታል ይባላል። ግን ወዴት ወዴት“ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል ይባል የለ” ያ ክፉ ቀን ወዴት የአሁኑ (?) ወዴት።

በዚያ ክፉ ቀን ህዝቡ በሞት የተሸነፉ ዘመዶቹን እየቀበረም እየጣለም እሱም ከሞት ጋር ግብግብ እየገጠመና በነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ እየተጣደፈ ከአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫ ወደ ንጉሱ ዓጤ ምኒልክ ቤተ-መንግስት በጥቁር እንግዳነት ከአሸለቱ ቁመናዎቹ ጋር የተገጠገጠው ችግረኛ ቁጥር እንዲህ ቀላል የሚባል አልነበረም። በዘመኑ ይህንን የሰቆቃ ትዕይንት በዓጤ ምኒልክ ቦታ ሆኖ ላየው ይጨንቃል አቅል ይሰውራል። ይሁን እንጅ ንጉሱ ከእውነቱ ዘወር አላሉም ይልቁኑም በተሰበረ ልብ እንዳመጣጡ ተቀበሉት እንጅ። እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ምንድነው ህዝብ የሚያምነው መሪ ሲያገኝ የአባት ያክል ያምነዋል። ህመሙን ፤ ጭንቀቱን፤ የሆዱን ብሶት ሊያካፍለው ይፈልጋል። ከእግዚአብሄር ቀጥሎ ህዝብ ልቡን የሚጥለው በእርሱ ላይ ነዋ!። ዓጤ ምኒልክ ይህ ግርማ ሞገስ በህዝባቸው ላይ ነበራቸው እምየ የሚለውን ስም ያገኙትም በነኚህ የጭንቀት ቀናት ነው ይላሉ ብዙዎቹ። ለሩህሩህነታቸውና ለደግነታቸው ከህዝብ የተሰጠ የፍቅር ስጦታ!።

ደጉ ንጉስ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ከባድማው የተሰደደውን መፃተኛ እንደዛሬዎቹ ጅቦችና ዘግቶ በላዎች፤ ሲቀጥልም የዘመናችን ኦውሮቦሮሶች፤ ክቡሩን የሰውን ልጅ በስቃይ ጅራፍ እይነረተ እመሬት ላይ ስለሚደባልቀው፤ ብሎም እነርሱ ራሳቸው ጎትተው ስላነገሱት የችጋር ጭራቅ መስማት እንደማይፈልጉት የአፍ ጉልበተኞች የመስቃን ቃል አልተናገሩም ፈሪሃ እግዚአብሄር አላ!። በእኔ የንግስና ዘመን ? የምን ርሃብ? ብለው የአካኪ ዘራፍ ምላስ አልወነጨፉም። ከዚህ ይልቅ በቅርባቸው ለነበሩት የሃይማኖት አባቶች እግዚአብሄር ምህረቱን ይልክ ዘንድ አጥብቀው እንዲለምኑ አሳስበዋቸው እሳቸው ግን ከዙፋናቸው ወርደው በእጃቸው የተገኘውን ያድሉ ገቡ። በአካልም በአስተሳሰብም የሸመገሉት ንጉስ ምኒልክ ያደረጉት ይህንን ነው።

የእኛዎቹ የዘመናችን አውሮቦሮሶች ግን በመለኮት እቅድ ምክኒያት ግንዘተ-ልቦና ሆኖባቸዋልና ክፉ ዘርን ይዘሩ ዘንድ በመርዝ በተሞሉ አለብላቢት ምላሶች ላይ በመቆማቸው፤ መልካም ዜና ከነርሱ ዘንድ ላይሰማ እነርሱ ለጸባዖት የራቁትን ያህል ለእነርሱም የራቀ ነው። ከዚያ ይልቅ በደደቢቱ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተው፤ ነገር ግን ጠረጴዛ ላይ ተፈትኖ ለመውጣት በምሁራን መካከል ለመገኘት የሚቅለሰለሰውንና የዓይን-ዐፋሩን የኢኮኖሚክስ ስሌታቸው የ”ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ድምር በሁለት አሃዝ ተመንድገናል እያሉ እንደልጅ ይቧርቃሉ። ወደ ጉልምስና የማይመጣ የተፈጥሮ ህግጋትን የናደ ውበት አልባው ልጅነት! ድንክየነት! ይሏል እንግዲህ ይህ ነው። ለዚህ ነው ታላቁ መጽሓፍ መጽሓፍ ቅዱስ “ንጉሶቿ ህጻናት ለሆኑ ለዚያች ሃገር ወዮላት” የሚለን በልጅነት አዕምሮ መጡ በልጅነት አዕምሮ አረጁ በልጅነት አዕምሮ ወደ መቃብር መውረዱን ተያይዘውታል። የሸመገለና የተፈታ ልብማ እርቅ እርቅ ይሸተዋል፤ ሁሉን የሚሸከምበት ሰፊ የፍቅር ቋት ይኖረዋል፤ ማንም ያለጭንቀት የሚያርፍበት የመንፈስ ጥላ ይኖረዋል።

ምድራችን ለቁጥር የሚታክቱ ለስልጣናቸው የሚንሰፈሰፉ ነገስታትንና አምባገነኖችን አስተናግዳለች ይሁን እንጅ የህዝባቸውንና የሃገራቸውን ክብር የሚነካ ጉዳይ ሲገጥማቸው ግን ሁሉም ማለት ይቻላል ግንባር ቀደም ሆነው ዘብ በመቆም አያስነኬዎች ናቸው። ከእነዚህም መካከል አንዱ አጤ ምኒሊክ ናቸው። ንጉሱ ስልጣን ይገባኛል ብለው ታግለዋል ተራራ ወጥተው ወርደዋል። በህዝብ ላይ ርሃብ በመጣ ጊዜ ግን ህዝቤ፤ ድሆቼ ብለው ከልብ በተሰበረ መንፈስ አነቡ አንጅ የተሟገገውን ገላ አይተው ጎሽ የኔ ልጅ በእኔ የንግስና ዘመን ጠግበኸልኛል ብለው የሳሳውን ገላውን በፕሮፐጋንዳ ሳማ አልገሸለጡትም። እንደ ወንጭት የተጠረበውን ባቱን አይተው እንዲያ እንጅ ጠብደሃል በል በሚል የግፍ ቃል አንገቱን አስደፍተው ባይተዋር አላደረጉትም።

እዚህ ላይ እንደ ዋቢ የምጠቅሰውና “እውነት” የሚለው ክቡር ቃል ይገልጠዋል ብየ የማስበው የሶፎክለሱ ንጉስ ኤዲፕስ ትዝ አለኝ። በእርሱ ዘመን የአቴናን ምድር ያንቀጠቀጠ አንዳች የመቅሰፈት ምች ከተማዋን ያደቅቃት ያልማት ጀምሯል ። ህዝቡም በደረሰበት አደጋ ተደናግጦ፤ ተጎሳቁሎና እንደሞት ሰራዊት በአስፈሪ ድባብ ታጅቦ ወደ ቤተ መንግስቱ ይተም ይዟል። ይህን የተረዳው እውነተኛውና አስተዋዩ ንጉስም ህዝቡን ለመቀበል ከነሞገሱ ወደ ሰገነቱ ይወጣል። በሚያየው ነገር ግን ልቡ ይናጥ ይደማ ጀምሯል። አይን-ስውሩን ነቢይ የዚህ መቅሰፍት መንስኤና መፍትሄው ምን እንደሆነ እንዲነግረው አጥብቆ ይጠይቀዋል። ከብዙ የዙሪያ ንግግርና ከሽማግሌዎቹ መዘምራን ምክር በኋላ ንጉሱ እውነቱ ካልወጣ መፍትሄ የለም በሚል እሳቤና ፤ እውነትንና ፍትህን በአደባባይ ለማቆም ቆርጦ በመነሳቱ ምክኒያት አውጫጭኙ ከሯል። ሁሉም ክርክሩ በፈጠረው ግለት በፍርሃት እየተለበለበ ጥግጥጉን ይዟል ይባስ ብሎም ንጉሱ ችግሩና መፍትሄው ካልተገኘ ደግሞ በየደረጃው ያሉትን ሃላፊዎችን ተገቢውን ቅጣት እንደሚያከናንባቸው ዛተ። የነገሩ ስር ከግራ ከቀኝ እየተቧካ በስተመጨረሻው ፍርጥርጡ ወጣና ንጉሱ የመርገሙ ምክኒያት ሆኖ ተገኘ። እዚህ ላይ ነው የኤዲፐስ ማንነት የሚታየው ከተጠያቂነት ለመዳን ልሸፍን ላዳፍን፤ ስልጣኔን ንግስናየን ላስጠብቅ አላለም በራሱ ላይ አስቃቂውን እርምጃ በመውሰድ ስልጣኑን ለቆ ከምቹው ቤተ-መንግስት በመውጣት የእውነትንና የፍትህን ጫፍ አሳየ። እዚህ ላይ ከንጉሱ አስገራሚ ባህሪዎች ሁለት ዋና ዋና ቁምነገሮችን ልናይ እንችላለን በመጀመሪያ ከኔ የተሻለ ዕውቀት ሌሎች ይኖራቸዋል ብሎ ማሰብና ሌላው ደግሞ እውነት እንዳትዳፈን መድከሙ ናቸው። የአቀባበላቸው ዳኝነት እውነት መሆኑ ደግሞ ሁለቱን ንጉሶችን አመሳሰለብኝ።

የመጣጥፌ ዋና ዓላማ የዘመናችንን አውሮቦሮሶች ጥላሸት በመቀባት የፖለቲካ ትርፍ በማግኘት በጭንቅ ውስጥ ባሉ ወገኖቼ ህይወት ላይ ቁማር ለመጫወት እንዳልሆነና ሰውን ያክል ክቡር ፍጥረት እንደሰው በስፍራችን መገኘት አቅቶን በነገር ዘባተሎ እየተጠላለፍን በወደቅንበት በዚያ ቁመናውም ልኩም በማይታወቅ የውዝግባችን ቅርቃር በመሸንቆር ያስተሳሰብ ብልግና ውስጥ ራሴን ለመጣል በመፈለግም አይደለም።

ጥያቄየ ግን እውነቱ ወዴት ነው? ነው። የርሃባችን አቢይ ምክኒያት ብዙዎቻችን እንዳልነው የቀኑ ክፋት ወይስ የገዥዎቻችን ክፋት? ወይስ እነሱ እንዳሉት ኤሊኖ?። ኤሊኖ! አይ ቅጥፈት! ነገ ደግሞ የሆነ ችግር ቢፈጠር የዚህ ችግር ዋና ምክኒያት የህዳሴው ግንባታ ያመጣብን ጣጣ ነው ሊሉን ይችላሉ ምን ችግር አለው? ባፈጠጠ የህሊና ጥሰት ለሚኖር እጓለ ምዑት ሰፈር እኮ ውሸት አንድ ሙዚቃ ነው። ምነው ገዥዎቻችን ራሱን እንደሚበላ አውሬ አረመኔነቱን አጦዙትሳ? የዚህ በለየለት የህዝብ የጠላትነት ጫፍ ላይ መቆም ጉዳይስ የሂሳብ አወራረዱን ምን ያስመስለው ይሆን?። ደግሞስ በዚሀ በሰለጠነ ዘመን ሰለ ርሃብ ማውራት አይቀፍም ወይ?። ለገባውማ ይቀፋል ይጎፈንናል እንጅ! ለደደቢት ምሩቃን ግን ይህ የመርህ ጉዳይ ነውና እንደ ታላቅ ስኬት ይቆጠራል።

በአጤ ምኒልክ ዘመን ከደረሰብን ርሃብ አርባ ዓመት ቀደም ብሎ በድንች ላይ ጥገኛ በነበረው የአየርላንድ ህዝብ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ርሃብ አየርላንዶቹ ታሪካቸውን በሃዘን የሚገልጡት ምዕራፋቸው ነው። “ The great famine” ተብሎ በተሰየመው በዚህ ርሃብ “The potato blight” የሚባል የድንች በሺታ ተከስቶ በሚሊዮን የሚቆጠር የአየር ላንድን ህዝብ አርግፏል አሰድዷል። ለዚያ ርሃብ በህዝቡ በኩል የቀረበው ምክኒያት በጊዜው በነበረው የአስተዳደር ብልሹነት ነው ሲል በሹሞቹ በኩል ግን የለም በጊዜው የተከሰተውን የድንች በሺታ ነው በሚል የተነሳው ውዝግብ ቀጥሎ ግን ሳይቋጭ እንደተንጠለጠለ የቀረ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጅ ያ የርሃብ ምች እንደኛ እያሰለሰ አዚም ላይሆን ዳግመኛም ተከሰቶ የአየርላንድን ህዝብ ላይቀጥፍ አሸልቦ በአየርላንዳዊያን ግብዓ- ተመሬቱ ተፈጽሟል። የእኛ የርሃብ አዙሪት ግን እኛኑ ሊቀብረን እየሰለለን ይመስላል እውነተኛውን መንሰኤውንና መፍትሄውን ገና አላገኘነውማ!።

በዚህ በምኖርበት በእስራኤል ሃገር እስራኤላውያኖቹ የሚሉት እኔንም የሚገርመኝ ነገር አለ። ይኸውም መሬታቸው በአብዛኛው አሽዋማ ነው ግን ይሰሩበታል፤ የተስተካከለ የዝናብ ወቅት የላቸውም እነርሱ በዚያም ጥገኛ አይደሉም፤ የመሬታቸው የቆዳ ስፋት ትንሽ ነው ግን ከሚበላው የሚደፋው ይበልጣል። እነርሱም በኩራት የሚናገሩት እዚህ ላይ ነው። “በካርታ ላይ እስራኤል ብሎ ለመጻፍ ቦታ እንደሌለ ሁሉ መሬታችንም ጠባብ ናት ግን እስራኤል ሃገር ርሃብ የለም።” ይላሉ።

ስለአንዱ የገጠር መሬታቸው ትንሽ ልንገራችሁ ትንሿ ገጠር יוטבטה’’ (ዮትባታ) ትባላለች በሃገሪቱ ደቡብ ምስራቃዊ ክፍል ትገኛለች። የዚህች መንደር መሬት አሽዋ ነው የመንደሯ ነዋሪዎች አርሰው ለማምረት ሲፈልጉ መጀመሪያ መሬቱን አጥበው ጨውን ማስወገድ አለባቸው ከዚያ በኋላ ነው ዘር የሚዘሩት ታዲያ የዚህች ትንሽ የገጠር መንደር ገበሬዎች በመላ እስራኤል የእርሻ ምርታቸውንና የወተት ተዋጾዖቻቸውን በማቅረብ ይታወቃሉ። እስኪ በስራኤል ዓይነት የእኛን ሁኔታ እንመልከት።

ወደ ጉዳያችን ስመለስ የዘንድሮው ጠኔ ገድ አልባ ሆኖና እንደ ቀላዋጭ እንግዳ ተሰልችቶ ነው ብቅ ያለው። በም ዕራባውያን በኩል ከሰራተኛው ህዝብ ከሚሰበሰበው ግብር እየተቆረሰ የሚላከው ገንዘብ የገዥዎቻችን የብልግና ጡንቻ ማፋፊያ እንደሆነና አውሮቦሮሶችም መናጢ ደፍቶ በላ ትዝቢዎች መሆናቸውን ከተገንዘቡ ውለው አድረዋል። እናም የሚራራው ልባቸው ተዘግቷል። እዚህ ላይ አንድ ገጠመኜን በምሳሌነት ላንሳ በስደት ከሃገሬ ከመውጣቴ በፊት በሙያየ ለአንድ መያድ (NGO) የ 30 ደቂቃ አጭር ተውኔት እንዳዘጋጅላቸው እየተነጋገርን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍው የኖርዌይ ልዑካን ቡድን ለግምገማ ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡበት ወቅት ነበር። ልዑኩ የስራ ግምገማውን ከጨረሰ በኋላ የደርሰበት ድምዳሜ ከሚንቀሳቀሱት ጣቢያዎች መካከል ሰባቱን መዝጋት መወሰኑን አሳወቀ ምክኒያቱስ ተብሎ ሲጠየቅ ልዑኩ የሰጠው አጭር መልስ “ የሃገራችሁ ባለጠጎች የሚይዟቸውን መኪኖች ስንመለከት በእኛ ሃገር በብዙ ሰዎች የማይያዙ ንብረቶች ናቸው እኛ ይህንን የኢትዮጵያ ፕሮጀክት ስናንቀሳቅስ ከድሆች እየለመንን ነው። በእኛ ግንዛቤ እነዚህ ባለጠጎቻችሁን በታግባቧቸው ይህን ፕሮጀክት ሊያንቀሳቅሱ ይችላሉ ብለን እናምናለን።” በማለት ውሳኔአቸውን አጸኑ።

አስተውሉ እነዚህ የኖርዌይ ሰዎች እየተናገሩ ያሉት ሰው ስለሚባለው ሰው ነው። ወገኖቹ በርሃብ ሲያልቁ ከአልጋው ወርዶ መሬት በመተኛት ያለውን ስለሚያካፍለው ሰው!። ከሚያማርጠው ውስኪ ወጣ ብሎ ለወገኖቹ አንድ ጣሳ ውሃ ማቅረብ ስለሚችል ሰው!። ልቦናውን እንደተሰረቀውና እንደ አለሌ የሜዳ አህያ ከሚፋንንበት ርቆና ከህሊናው ጋር ታርቆ ስለሚኖረው ሰው!። በነርሱ ሃገር የህሊና ግዴታ የሚባል ነገር አላ!። ይህማ ባይሆን ከሃገራቸው ኢትዮጵያ ድረስ ምን አንከራተታቸው?። እነዚህ እንግዶች የኢትዮጵያ ባለጠጎች ይሳተፉ ማለታቸው በሰው ውስጥ ሊኖር የሚገባውን ህሊና መሰረት አድርገው ነው። ህሊናውን በጣለ የወዲኒ መንጋ መካከል መኖራቸውን አላወቁም ነበር።

የወደቅንበትን እናስተውል የማዕድ በጀት አልባ ሆኖ በቆሻሻ ገንዳ ከውሻ እና ከአሞሮች ጋር እየተናጠቀ ጉሮሮውን ዘግቶ በሚያድርባት ሃገር ሌላው የሁለት ሚሊዮን ብር ይዞ ሲንፈላሰስ የህሊና ህግ ስለተጣሰ አይጠየቅም!። የፋራ ነው!። ውሃ ባአግባቡ ማቅረብ ባልቻለች ሃገር ውስጥ ጥቂቶች ውስኪ እንደ ውሃ የሚራጩባት የጉድ ሃገር መሆንዋን ስናይ የሰው ያለህ ብለን በባይተዋርነት እንንገደገዳለን። ምንጩ ሲመረመር ደግሞ አይን ያወጣ ሌብነት በሃገሪቱ በመንሰራፋቱ ነው። የወረድንበት የዝቅጠት ልክ ሲለካ አራዊትን እንኳን አልመጠነም ቀልለን ተገኜን። ምን ማለቴ ነው በቡድን የሚጓዝ የአራዊት መንጋ ዞጉን አይነካም ነውር ነው ህገ-አራዊት ወሰናይ አላቸውና! ቢጣሉ እንኳን አይገዳደሉም ። ኃይላቸውን ለሌላው ባላንጣቸው ይጠብቁታል እርስ በርሳቸው ቢገዳደሉ ለነገ የመኖር ዋስትና እንደሌላቸው ያውቁታል ይህ ዕውቀት አላቸው። ያደኑትን ተካፍለው ይበላሉ ከመሃከላቸው አውራ የተባለው እንኳን ኃላፊነት ተሰምቶት ከርሱ ለሚያንሱት ትቶላቸው ዘወር ይላል። ሃገራችን ግን በአውሮቦሮሶች ተውርራለች።

በግሪካውያን ጥንተ-እምነት ጥናት መሰረት አውሮቦሮስ የሚባል የድራጎን አይነት ነበር። ፕሌቶ ስለዚህ ዝርያ ሲናገር “ዝርያው ዓይን ስለሌለው አድኖ የሚበላውን አያይም ፤ ጆሮም ስለሌለው አዳምጦ የሚጎመርበት ፍጥረት የለም አፈርና ውኃ ሲልስ አድጎ በመጨረሻ ከጅራቱ በመጀመር ራሱን እየበላ ወደ ግብዓ- ተመሬቱ ያዘግማል። እናም ፕሌቶ ስለዚህ አሳዛኝ አውሬ ሲደመድም ራሱን የሚበላ ፍጥረት በዚህች ምድር ህልውና የለውም።’’ ይህን የድራጎን ዘር ከእኛዎቹ ወዲኒዎች ጋር ያመሳሰልኩበት ምክኒያትም የሚሰሙበት ጆሮ የሚያዩበት ዓይን ስለሌላቸው ነው። ያላቸው አፍ ብቻ ነው። ያ ነው ጉልበታቸው። ያንም ህዝባቸውን ለመብላት እየተጠቀሙበት ነው ሌላውን ለማሸነፍ አፍ ብቻውን ጉልበት አይሆንም ። ግን ርቀቱ እስከየት ነው?። ህዝብ በስደት ውኃና በርሃ እየበላው አንድ ወፍ የሞተ ያክል እንኳን የዚያን ህዝብ ዕልቂት ከቁብ አይቆጥሩትም የዕልቂቱ ምክኒያትም እነርሱ መሆናቸውን ባለመቀበል በክህደት ይደመድሙታል። ከዚህ በላይ የራስን ህዝብ ራስንም ከመብላት የበለጠ አረመኔነት በየትኛው ፍጥረት ይታያል?። 15 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ ውሸት ነው ብለው በፕሮፐጋንዳቸው ለማፈን ተሯሯጡ በርሃብ እየተጠበሰ ካለው ህዝብ ይልቅ የእንቧይ ካብ ስልጣናቸው በልጦባቸው በተራበው ህዝብ ላይ ቀለዱ። ይባስ ብለው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በመበጀት ህወሐትና ብአዴን (EPRDF) ለአስረሽ ምቺውና ለሴሰኝነታቸው ማስገሪያ እየበተኑ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ዜጋ በሚል ፈሊጥም ፊታቸውን በአሞሌ ታጥበው ለአንድ ሰው 25 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ቤት እየሰሩ እንደሆነ ነግረውናል። እነዚህ ሰዎች የህዝብን ገንዘብ ሰርቀው የግላቸው ሲያደርጉ ኢሞራላውነትና ኢሰብዓዊነትን እያነገሱ ነው ይህንም ሲያደርጉ ህዝብንም ትውልድንም እየበሉ እንደሆነ አላወቁም ትውልድን ሲበሉ ራሳቸውን እየበሉ መሆኑንም ገና አልተገለጠላቸውም ። ከዚህ በላይ በህዝብ ላይ ንቀትና ጥላቻስ በምን ይገለጣል?። የናረ የህዝብ ጠላትነት!። ግን አንድ ነገር እመኛለሁ ደብቶ ከያዘን ከዚህ አዚም ስንወጣ! ያኔ ለጠላቶቻችን ዕድሜ የሰጠናቸው እኛ መሆናችን ሲገባን ራሳችንን እንወቅሳለን።

The enemy of the people (የህዝብ ጠላት) ከሚለው የኢብሰን ተውኔት ትንሽ ማለት ፈለግሁ። በኢብሰን ተውኔት ውስጥ ከህዝብ ጎን በቆመው ሃኪም እና በህዝብ ጠላትነት በቆመው የከተማዋ ከንቲባ ገጸ፟-ባህሪያት መካከል ያለውን ፍትጊያ በአጭሩ ስናይ ሃኪሙ የከተማዋን ነዋሪ እያረገፈው ያለውን ሞት ምክኒያት ለማወቅ ሲወድቅ ሲነሳ ይቆይና ምክኒያቱን ያገኘዋል ያም የከተማዋ ህዝብ የሚጠቀምበት ውኃ በመመረዙ ነው። ሃኪሙ መንስኤውን በማግኘቱ ትንሽ ተደስቶ ወደ መፍትሄው ሲዞር ደግሞ መፍትሄ ብሎ ያገኘው የከተማዋን ህዝብ ወደ ሌላ ስፍራ ማዞር ነው ይህንንም ለከተማዋ ከንቲባ ያማክረዋል። የከተማዋ ከንቲባም ለሃኪሙ ምክኒያቱንም መፍትሄውንም እንዳይናገር ይከለክለዋል ይባስ ብሎ በከተማዋ ከሚገኘው ታዋቂ የጋዜጣ ኤዲተር ጋር በመመሳጠር የፕሮፕጋንዳውን ስራ ያጧጡፉታል። ለህዝቡ ሞት ደንታ ያልሰጠው ከንቲባ የሃኪሙንም የመናገር መብቱን ከለከለው። የከንቲባው ዋና ዓላማ ህዝብ አይደለም ስልጣንን ማስጠበቅ ነው ለዚህም የፕሮፕጋንዳውን ስራ ማጧጧፍ ነው። ትንቅንቁ ይቀጥላል። የህዝብ ጠላት የሆኑ ሹሞች ጉዳያቸው ከስልጣናቸው ጋር እንጅ ከህዝብ ጋር አይደለም ይህ ስራቸው ደግሞ በህዝብ ጠላትነት ጎራ ያስፈርጃቸዋል። ቸር ያገናኘን።

በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል * ፊደል ቀመስ አባሎች ውጤቱን አልተቀበሉትም

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ የግንቦት15ቱን ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉ ከተገለጸ በሁዋላ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል። ምንጮች እንደገለጹት በርካታ ፊደል ቀመስ አባሎቹ ኢህአዴግ አሸነፍኩ
ያለበትን የድምጽ ልዩነት አልተቀበሉትም። ውጤቱን የሚቃወሙ የግንባሩ አባላት ” ህዝቡ ከእንግዲህ በሰላም መንግስት እቀይራለሁ የሚለው እምነቱ ተሟጦ የሃይል አማራጭን ብቻ እንዲመለከት ከማድረጉም በላይ፣ የሃይል አማራጭን
የሚከተሉ ሃይሎች በህዝቡም ሆነ በአለማቀፉ ማህበረሰብም የተሻለ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል” በማለት ለድርጅቱ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
election 2015
በሌላ በኩል ደግሞ ተገኘ የተባለውን ውጤት ከመደገፍ አልፈው፣ ህዝቡ እንዴት ለተቃዋሚዎች ይህን ያክል ድምጽ ሊሰጥ ቻለ በማለት በቁጭት አስተያየት የሚሰጡ ደጋፊዎች መኖራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።

ኢህአዴግ እያሰባሰበ ባለው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፣ አንዳንዶች ” ይህ ህዝብ ምን አይነት ልቡ የማይታወቅ ከሃዲ ህዝብ ነው! እንዴት ይሄን ሁሉ ልማት እያዬ ለተቃዋሚ ድምጹን ሊሰጥ ቻለ?” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫ ቦርድ ራሱ ባወጣው ሰሌዳ መሰረት የምርጫውን ውጤት መግለጽ የነበረበት ግንቦት21 ቢሆንም፣ የግንቦት20 በአልን ለማድመቅ እንዲረዳ በሚል ከእቅዱ በፊት እንዲገለጽ መደረጉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ
ዘጋቢያችን ገልጿል።

ኢህአዴግ በየክልሉ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የፌሽታ በዓላትን አዘጋጅቷል። ትናንት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አርቲስቶች ያዘጋጁት የኪነጥበብ ምሽት በብሔራዉ ቲያትር ተካሂዷል፡፡፡ በርካታ የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች በተለያዩ ሆቴሎች
በዓሉን ለማክበር ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግን አሸናፊነት ቢያውጅም መድረክ የተባለው የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የምርጫውን ውጤት አልተቀበለውም። ድርጅቱ ምርጫው አነስተኛ የሚባሉ መስፈርቶችን እንኳ ያላሟላ በማለት አጣጥሎታል። መድረክ
በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ገለልተኛ የሚባሉ ሰዎች ተመርጠው መምርራ እንዲያካሂዱ ጠይቋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫውን በተመለከተ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ያለው ነገር የለም። መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎችን እያዋከበ በማሰር ላይ መሆኑ፣ ፓርቲውን አጣብቂኝ ውስጥ ሳይከተው አልቀረም። ሰማያዊ የምርጫውን
ውጤት ይቀበለዋል ተብሎ አይጠበቅም።

የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን በተመለከተ በርካታ እጸጾችን አውጥተው ቢገልጹም፣ ከኢህአዴግ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቶች
በምርጫ ታዛቢነት እንዳይሰታፉ መከልከላቸው፣ ምርጫው አሳታፊ አለመሆኑንና የተለያዩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መታሰራቸውን በመግለጫቸው አመልክተዋል።

በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ በርካታ አስገራሚ ክስተቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። ግንቦት12 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ልዩ ቦታው ላንቻ ወይም ጠመንጃ ያዥ ነዋሪ የሆነ አንድ የ12 ዓመት ህፃን የኢህአዴግን የምርጫ መልዕክት ያየዘ
ፖስተር ከተለጠፈበት ግድግዳ ላይ ቀደሃል በሚል 6 ወር ተፈርዶበታል።

በአዲስ አበባ ችሎት በሚባል ቦታ አርብ ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ሁለት ማየት የተሳናቸው ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ወጣቶቹ የተያዙት አንደኛው ሙሉ ሰማያዊ ልብስ ለብሶ በመውጣቱ በተፈጠረው አተካራ ነው። የአካባቢው
ሴት ካድሬ አንደኛውን ማየት የተሳነው ወጣት “ለምን ሰማያዊ ልብስ ለበስክ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነሆይ?” በማለት ጥያቄ ስታቀርበለት፣ ጓደኛው “ምን አገባሽ ምንስ ብለብስ!” የሚል መልስ መስጠቱን ተከትሎ፣ ግለሰቧ በብስጪት
ለደህንነቶች ባስተላለፈችው ጥቆማ መሰረት ሁለቱም ወጣቶች በድንገት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ ታስረው ይገኛሉ።
መነን መሰናዶና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ፀሃይ ጮራ ት/ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 20 መምህራንና 30 ተማሪዎች የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል ዝርዝራቸው ለጸጥታ አካላት ተልዕኮ በልዩ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከምርጫ በፊት ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

– See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/41803#sthash.rXRMye6y.dpuf

የወያኔ መንግስት በመላው አዲስ አበባ በታንክ የተደገፉ ታጣቂዎችን ማሰማራቱ ተነገረ *በለምለም ከበደ*

May 20, 2015 Leave a comment

ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ በባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ  በማስፈራራት ጀምሮአል። በምርጫ ቅስቀሳ የፈራው የወያኔ መንግስት ፓርቲዎችን በክርክሩ መርታት ሲሳነው በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ አይተናል በክርክሩ የህዝብ አመኔታን ያጣው ገዢው ወያኔ የሚጨብጠው ቢያጣ ንቢቱን ተመስሎ በተሰራ ባለ ጎማ ታንክ በከትማይቱ ላይ ይደነፋ ጀምሮአል ድሮም ኮሮጆ በመስረቅ  ነው 25 ዓመት በሃይል የገዛው ።

ገዥው የወያኔ መንግስት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አምስተኛው የኢትዬጲያ ብሄራዊ ምርጫ ግይካሄዳል ፡፡ ሶስተኛውና ተስፋ የፈነጠቀው አገራዊ ምርጫ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የፓለቲካ ምህዳር መዘጋት ከተጠናቀቀ በኋላ የተካሄደውን አራተኛው ምርጫ ኢህአዴግ 99.6  በመቶ የፓርላማ መቀመጫ “በማሸነፍ” ተቆጣጥሮታል፡፡  ከቀናት በኋላ የሚካሄደው አምስተኛ አገራዊ ምርጫ የፓለቲካ ምህዳሩን ለማሻሻል የሚረዳና መጠነኛ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም በተቃራኒው ገዥው ፓርቲ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያዳከመ ተቺዎችን እና ሌሎች ነጻ ድምጾችን ለእስር ዳርጎ በከፍተኛ ጫና ታጅቦ ይካሄዳል፡።

የወያኔ መንግስት ህዝብን ማስተዳደር የማይችል አሸባሪና ዘረኛ ፓርቲ ነው። የኢትዮዽያ ህዝብም አንቅሮ ከተፋው ቆይቷል ወያኔም የተረዳው መሆኑን በሰሞነኛ ድርጊቱ እየታየ ነው። አንዳንድ የአፍሪካ አንባገነን መንግስታት ሽንፈታቸውን በሃይል ለምቀበል የሚደረገው ሙከራ ወያኔ ከምርጫው ቀድሞ ወታደሩን እና ታንኩን በአደባባይ ኮልኩሎ ህዝብን ማሸበር የተሸናፊነት ምልክት መሆኑን አውቀናል።

ወያኔ ተንቦጫብጯል ወያኔ ፈርቷል እንደለመደው የህዝብን ድምጽ ሊሰርቅ አሰፍስፋል ለተከታይ ፭ አመት የህዝብን በዘረኛ እና በግፍ አገዛዝ ሊገዛ አሰፍስፎ በማስፈራራት ታንክ ጭምር ከተማ ላይ በማሰማራት የህዝብን ድምጽ ለመገደብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ስለዚ የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃ በቃ በቃ በቃ በማለት ይህን የዘረኛ መንግስት በአንድነት ልናስወግድ ይገባል።

ሞት ለወያኔ
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር

spacer height=”20px”]

 

 

 

 

BBN የኢቲቪ ድራማ ፤የታክሲ ላይ እሰጥ አገባ የድምጻችን ይሰማ ሳንቲም መሰብሰብ መርሃግብር ተጽእኖ እየታየ ነው

Fikre-Tolesaspacer height=”20px”]

 

 “የጀግኖች እናቶቻችንን እና አባቶቻችንን ፈለግ እንከተል!” – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፭

ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርገዋት የኖሩት ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር፣ ሕይዎታቸውን ለሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር እንዲሁም ለወገኖቻቸው ነፃነት ሲሉ ሲገብሩ የኖሩ ጀግኖች እናቶች እና አባቶች ስለነበሩን ነው። ከ፸፬(ሰባ አራት) ዓመታት በፊት ፋሽስት ጣሊያንን ያንበረከኩት የዛሬው ትውልድ ወላጆች እና አያቶች፣ ከሁሉም የሚበልጠው የጽናታቸው ምንጭ፣ ለአገራቸው ነፃነት የነበራቸው ቀናዒነት ነበር። ነገር ግን «የእሣት ልጅ ዐመድ» ሆኖ፣ በእኛ ትውልድ ዘመን እነርሱ በብዙ ልፋት እና ትግል የገነቧት ኢትዮጵያ በመፈራረስ ሂደት ላይ ናት።
moresh
በአምሥቱ ዓመት የአርበኝነት ዘመን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን «ዱሩ ቤቴ» ብለው የፋሽስት ጣሊያኖችን እና የእነርሱ ባንዳዎች የነበሩትን ከሃዲዎች ጥምር ጦር ተፋልመዋል። በኅዳር ወር ፲፱፻፳፯ ዓ.ም. ኦጋዴን ውስጥ ወልወል ወደተባለው የኢትዮጵያ ግዛት የፋሽስት ጣሊያን ወታደሮች ዘልቀው በፈጠሩት ትንኮሣ የተጀመረው ጦርነት፣ ከአምሥት ዓመታት በላይ ወስዶ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ በድል አድራጊነት አዲስ አበባ ሲገቡ ወረራው ተቀልብሷል። በእኒያ አምሥት የአርበኝነት ዓመታት፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይ ዐማሮች፣ በግፍ ተጨፍጭፈዋል። በአሁኑ የገንዘብ ስሌት ሲተመን በቢሊዮን ብሮች የሚገመት ንብረት ወድሟል። ውድ እና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶች ተዘርፈዋል፣ ወይም እንዲወድሙ ተደርጓል። ይህ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለው ክቡር የሆነውን የአገርን ነፃነት ለማስመለስ ነበር፣ ጀግኖቹ የዚያን ዘመን ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነቱን ከፍለው አድርገውታል!

ከተለያዩ የታሪክ ድርሣናት እና መጻሕፍት ለማመሣከር እንደሚቻለው (ደጃዝማች ከበደ ተሰማ በ፲፱፻፷፪ ዓ.ም. «የታሪክ ማስታወሻ»፣ ዶ/ር ተወልደ ትኩዕ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. «የኢትዮጵያ አንድነት እና ኢጣሊያ»፣ ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. «የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983»፣ ገብረወልድ እንግዳወርቅ በ፪ሺህ ዓ.ም. «ማይጨው፣ የማይጨው ዘመቻና የጉዞ ታሪክ»፣ አምባሳደር ዘውዴ ረታ በ፪ሺህ፬ ዓ.ም. «የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት»፣ ፕሮፌሰር መሥፍን ወልደማርያም በ፪ሺህ፭ ዓ.ም. «መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ») ለማመሣከር እንደሚቻለው፣ በአምሥቱ ዓመት የፋሽስት ጣሊያን የወረራ ዘመን ከፍተኛውን መስዋዕትነት የከፈሉት አርበኞች በስፋት ይንቀሳቀሱ የነበሩት በተለይ፦ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በጎንደር እና በወሎ ክፍለሀገሮች ነበር። ከእነዚያ ስመጥር የአርበኞች መሪዎች መካከል ለአብነት ያህል የሚከተሉት ይገኙበታል።

· በሸዋ፦ አቡነ ጴጥሮስ፣ መላከፀሐይ ኢያሱ (የልጅ ኢያሱ ልጅ እና የሸዋ አርበኞች መሪ፣ አበበ አረጋይን ራስ ብለው የሾሙ)፣ ራስ ደስታ ዳምጠው (በሲዳሞ ግንባር ያዋጉ እና በጉራጌ አውራጃ በፋሽስቶች ተማርከው የተገደሉ)፣ ራስ አበበ አረጋይ (መንዝ፣ ተጉለትና ቡልጋ፣ ምንጃር)፣ ራስ መስፍን ስለሺ፣ ደጃዝማች አበራ ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች አስፋው ወሰን ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ወንደወሰን ካሣ (ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ባልቻ ሣፎ (በጉራጌ)፤ ደጃዝማች ፍቅረማርያም አባተጫን፣ ደጃዝማች አውራሪስ (መሐል ሸዋ)፣ ደጃዝማች መንገሻ ወሰኔ (መሐል ሸዋ)፣ ደጃዝማች ፀሐዩ እንቆሥላሤ (መርሃቤቴ እና ሰላሌ)፣ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ (ጅባትና ሜጫ)፣ ደጃዝማች ከበደ ብዙነሽ (ጅባትና ሜጫ)፤ ደጃዝማች በቀለ ወያ (በጉራጌ)፤ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ልጅ ኃይለማርያም ማሞ፣ ወይዘሮ ሸዋረገድ ገድሌ፣

· በጎጃም፦ ራስ እምሩ ኃይለሥላሴ (የጎጃምን እና የጎንደርን ጦር መርተው በሽሬ ግንባር ያዋጉ)፣ ራስ ኃይሉ በለው (ሞጣ)፣ ቢትወደድ አያሌው መኮንን (ባህርዳር-አቸፈር)፣ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ (አቸፈር እና አገው ምድር)፣ ደጃዝማች አበረ ይማም (ባህርዳር፣ አቸፈር እና ሜጫ)፣ ደጃዝማች ነጋሽ በዛብህ (ቡሬ ዳሞት)፣ ደጃዝማች ደስታ እሸቴ (ደጋ ዳሞት)፣ ደጃዝማች ኃይለኢየሱስ ፍላቴ (ደጋ ዳሞት)፣ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ (ብቸና)፣ ደጃዝማች መንገሻ አቦዬ (ሞጣ፣ ትውልዳቸው አልቡኮ (ወሎ))፣ ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ፣ አአቶ ጌታሁን ተሰማ (በኋላ ሚኒስትር እና አምባሣደር)፤

· በጎንደር፦ ደጃዝማች ዮሐንስ እያሱ (የልጅ እያሱ ልጅ፣ እና የቤገምድር አርበኞች አስተባባሪ)፣ ቢትወደድ አዳነ መኮንን፣ ቢትወደድ ገሠሠ ረታ፣ ራስ ውብነህ (አሞራው) ተሰማ፣ ደጃዝማች ዳኘው ተሰማ (ጎንደር፣ ቤገምድር)፣ ደጃዝማች ብሬ ዘገዬ፣ ደጃዝማች ታደሰ ይማም፣ ደጃዝማች ጀምበሩ፣ ደጃዝማች ገብሬ ካሣ፣ ፊታውራሪ ሥዩም ነጋሽ፣ ፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁን(አባ ከንትር)፣ ፊታውራሪ አለማየሁ ቢተዋ (ጭልጋ)፤

· በወሎ፦ ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ (በላስታ)፣

· በባሌ፦ ደጃዝማች በየነ መርዕድ፤

· በሐረርጌ (ኦጋዴን)፦ ግራዝማች (በኋላ ደጃዝማች) አፈወርቅ ወልደሰማዕት፤

· በኢሉባቦር፦ አቡነ ሚካኤል፤

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ያልተካተቱ አያሌ አርበኞች አሉ። ለወደፊት እያጣራን በስፋት እንዘግብበታለን።

ከፋሽስት ጣሊያን ጦር ጋር ሲፋለሙ የነበሩት አብዛኞቹ ጀግኖች እናቶች እና አባቶች ዛሬ በሕይዎት የሉም። ከመቃብር በላይ የሚውል ሥራቸው ግን ለዘለዓለም በትውልድ ሲዘከር የሚኖር ነው። ለመሆኑ እኒያ ጀግኖች ዛሬ ከመቃብር ተነስተው የትግሬ-ወያኔ የሚያመሰቃቅላት አገራቸው ኢትዮጵያ ያለችበትን እጅግ አሣፋሪ የታሪክ ምዕራፍ ቢመለከቱ ምን ይሰማቸው ይሆን? መቼም በምንም ተዓምር የባንዶች ልጆች እና የልጅ-ልጆች የሆኑት እነ መለስ ዜናዊ፣ ስብሐት ነጋ፣ ወዘተርፈ የሚያፈራርሷት የኢትዮጵያ ሁኔታ ሐሴትን ሊያቀዳጃቸው በፍጹም እንደማትችል ማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የሚገነዘበው ነው። ስለዚህ በእኛ ስንፍና እና ቸልተኝነት አገራችንን ለዚህ የታሪክ ውርደት ያበቃነው የአሁኑ ትውልድ፣ ለተተኪው ትውልድ የባሰ ችግር ከምናወርሰው፣ ቆም ብለን ያለፍንበትን የስህተት ጎዳና እንመርምር፣ ጊዜው ሣይጨልምብንም እናርመው!

ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

 

 

 

 

semayawi

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳያደርግ ከለከለ (ደብዳቤውን ይዘናል) »

09:42 am | • ‹‹ተቀባይነት የሌለው ተልካሻ ምክንያት ነው›› አቶ ዮናታን ተስፋዬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል…

May 6 2015 / Read More »

“የጀግኖች እናቶቻችንን እና አባቶቻችንን ፈለግ እንከተል!” – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት »

09:31 am | ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ ሚያዝያ ፳፯ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፲፭ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አድርገዋት የኖሩት…

May 6 2015 / Read More » የሰሜን ጎንደር ሕዝብ አመጽ በርትቷል * በድንበር ከተሞች አሁንም ችግሩ እየሰፋ ነው »

09:18 am | ምንሊክ ሳልሳዊ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው በሕወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ተወካዮች መሪነት በባህር ዳር ስብሰባ መቀመጣቸው በታወቀበት በዚህ ሳምንት…May 6 2015 / Read More » የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ »09:16 am | የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ትናንት ሚያዝያ 27/2007 ዓ.ም ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት…May 6 2015 / Read More » የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች የስር ተላላኪዎቻቸውን ሕዝቡ ኢሕአዴግን እንዲመርጥ አልቀሰቀሳችሁም በሚል ከሃላፊነታቸው ማውረዳቸው ተዘገበ »11:39 pm | የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር ሆነው ሲያገለገሏቸው የቆዩትን ሰዎች; ህዝቡን ኢህአዴግን እንዲመርጥ በሚያስችል መንገድ አልቀሰቀሳችሁትም በማለት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው እንደሆኑ…

May 4, 2015

ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት

London_Ethiopian_Church-300x178

የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እና አማራን በጠላትነት በመፈረጅ አከርካሪውን ሰብረነዋል በማለት በእብሪት ሲለፍፉ የነበሩት የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ወያኔ) ባለሥልጣናትና ደጋፊዎች በአሁኑ ወቅት ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነት ተቆርቋሪና አሳቢ ነኝ በማለት በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፋፋይ የጥፋት ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ከመንስዔው በቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብና በሃገሪቱ የቻሪቲ ሕግ መሠረት ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ መፈታት ሲችል የቤተ ክርስቲያኗ አባላትም ሆኑ ሕግና ደንብ አይገዛንም ያሉ ጥቂት ካህናት ሕዝብን ከድተው ለወያኔ ሹመኞች በባንዳነት አደሩ።በለስ ቀናኝ ያለው ወያኔም ሕዝብን የከዱትን ባንዳዎች በመጠቀም ስደተኛው ሕዝብ በሃብቱና በጉልበቱ ገዝቶ ያቆመውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመውረስ የራሱና የደጋፊዎቹ ለማድረግ በሁሉም ዘርፍ እንቅስቃሴ ጀመረ።በእነ አባይ ፀሐዬ ትዕዛዝና ቁጥጥር የሚንቀሳቀሱ ጳጳሳትን ወደ ውጪ በመላክ ቤተ ክርስቲያኗን ከነንብረቷ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እንዲንቀሳቀሱ አደረገ።
አልበገሬዎቹ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ግን ለሁለት ዓመት በዓላማቸው ጸንተው በመታገል ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በማቅረብ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነውን ቤተ ክርስቲያኗን በእኩል የመጠቀም መብታቸው እንዲጠበቅላቸው አስፈረዱ።በዚህ የተደናገጡት የወያኔ ሹማምንቶች የእንግሊዝን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ባለመቀበል የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ የሚቀለበስ መስሏቸው የወያኔው ጳጳስ ሳይቀሩ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት መሳቂያና መሳለቂያ ሆኑ።በዚህም አላበቃም በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚመራው መንግሥት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም አስነዋሪውን ሰላማዊ ሰልፍ ግንባር ቀደም ዜና በማድረግ አቀረበው።ይህም ወያኔ በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ለማመን ያዳግታቸው ለነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች ተገቢ ማረጋገጫ ነበር።
የኢትዮጵያው ቴሌቪዥን ስለ ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ያሰራጨውን ዜና የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ።

https://www.youtube.com/watch?v=07pqDgif7BI

በቅጥፈትና በክህደት የቆሸሸው የሃሰት ቋቱ ወያኔ፤ ሃገር ያወቀውን፤ ፀሐይ የሞቀውን ጉዳይ ዓይኑን በጨው ታጥቦ

• የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቀረበለት ከእውነት የራቀ አቤቱታ ላይ ተመርኩዞ ፈረደ ይላል፤
• በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩትን የቤተ ክርስቲያኑን አባላት የተለየ ዓላማ የያዙ ጥቂት አባላት ናቸው ይላል፤
• ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጣሰ፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ፈረሰ ይላል፤ (እግዚአብሔር ያሳያችሁ ወያኔ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተቆርቋሪ ሆኖ)
• ቤተ ክርስቲያኗ ከዓላማዋ በእጅጉ ለተለየ ተግባር ልትውል ነው ይላል፤ (ወያኔን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጉዳይ በእጅጉ አሳስቦት)

ውድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮችና ወዳጆች። ለሃይማኖታቸው፤ ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለመብታቸው ጸንተው የታገሉት የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት ሃሰት የተጠናወተው ወያኔ እንደሚለው ሳይሆን እውነቱ ሌላ ስለሆነ አባላቱ በፍርድ ቤት ፍትሕ ካገኙ በኋላ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በመግባት የሆሳዕና በዓልን ሲያከብሩ የሚያሳየውን ቪድዮ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ተመልከቱና ወያኔ የአጸያፊ ውሸትና ቅጥፈቱ ማሰራጫ ካደረገው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካስተላለፈው ነጭ ፕሮፓጋንዳ ጋር በማነጻጸር እውነታውን ተረዱ። http://londondebretsion.org/

ከዚህም በማስከተል የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (TPLF) ሹማምንቶችና ወኪሎች የለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላትን ከድተው ለወያኔ በባንዳነት ያደሩ ጥቂት ካህናትን በመያዝ የሚነዙት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ፋይዳ ቢስ ስለሆነባቸው በአሁኑ ወቅት ደግሞ በወያኔ ወኪሎች የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማስተባበር በለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ እንዲዘምቱ ለማድረግ አስተባባሪ ግብረ ኃይል አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን በየ አብያተ ክርስቲያኑ በሚያሰሙት አዋጅ ለማረጋገጥ ተችሏል።

ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የወያኔውን ሹመኛ ሙሉ ቃል ያድምጡ።

https://www.facebook.com/teshetu1/videos/o.332324390123167/1025781290785071/?type=2&theater

ከዚህ በማስከተልም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መራሹ መንግሥት የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ትግል ለማዳከም ወደ ውጪ ሀገራት የሚልካቸው ካድሬዎቹና ባለሥልጣናቱ ምንም ሳይፈይዱ ተዋርደው እየተመለሱ ስለተቸገረ በአሁኑ ወቅት የተያያዘው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትንና የቤተ ክርስቲያን ሹማምንትን በማሰማራት በሃይማኖት ሽፋን እነሱ ያቃታቸውን ተግባር እንዲያከናውኑለት ማድረግ በመሆኑ በዚህ መሠረት በአሁኑ ወቅት አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ የተባሉ ሁለት ጳጳሳት የወያኔ ባለሥልጣናትና ካድሬዎችን ሥራ ለማከናወን ለንደን ዩናትድ ኪንደም ገብተው ይገኛሉ።

london-church3-628x319

እንደ እግዚአብሔር ትዕዛዝና እንደ ክርስትና ሃይማኖት ቢሆን ኖሮ “የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላሉና” (ማቴ፡ 5:9) ተብሎ እንደተገለፀው በክርስቲያኖች መካከል ችግር ሲፈጠር እነዚህ ሁለት ጳጳሳት ሰላምና እርቅን ለማምጣት በጸሎትና በልመና በአማላጅነትና በአስታራቂነት በደከሙና በጣሩ ነበር።

እነሱ ግን በፁእ የሚለውን ማዕረግ ከመያዝ ባለፈ ተግባር የለባቸውምና ለንደን ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ከዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት ወደሚያመቿቸው የገብሬኤል እና የሥላሴ ቤተ ክርስቲያናት በመሄድ ከወያኔ ሹማምንቶች ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሃይማኖትንና መንፈሳዊ አገልግሎትን በሽፋንነት በመጠቀም የሁለቱን ቤተ ክርስቲያናት አባላት በማስተባበር ላለፉት 24 ዓመታት ከማንኛቸውም የወያኔ ሥርዓት ተጽዕኖ ነጻ ሆና በኖረችው የለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን እላይ የጥቃት ዘመቻ ከፍተው ይገኛሉ።አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ ለንደን ከሚኖሩ የወያኔ ካድሬዎችና የኤምባሲ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ካከናወኗቸው ወያኔያዊ ተግባራት ውስጥ፡1ኛ) የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ህንጻ ተከራይተው ጳጳሳቱ በተገኙበት በሊቢያ በረሃ መስዋዕት ለሆኑት ኢትዮጵያኖች ጸሎተ ፍትሐት ይካሄዳልና ሃዘኑ የተሰማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይገኝ በማለት የማታለያ ጥሪ አሰራጩ።በወገኖቹ ላይ የተፈጸመው አረመናዊ ድርጊት ያሳዘነውና ያስቆጨው ኢትዮጵያዊ ሃዘኑን ለመግለጽ በቦታው ላይ ሲገኝ እነሱ ግን የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አምባሳደር እና ሌሎች የወያኔ ባለሥልጣናትን የክብር እንግዳ በማድረግ በግፍ የፈሰሰውን የወገኖቻችንን ደም ስደትን በኢትዮጵያ አንግሶ ወገኖቻችንን የአረመኔዎችና የባህር ሰለባ በማድረግ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የአለም መዛበቻ ያደረገው የወያኔ አገዛዝ የፖለቲካ መጠቀሚያ መድረክ ሊያደርጉት ችለዋል።በግፍ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያንን ደም ጳጳሳቱ ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመሆን ለፖለቲካ ፍጆታ ካዋሉበት ሂደት የተወሰድ ምስል።በዚህ ምስል ውስጥም ወያኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን በግፍ ሲገድልና ሲጨፈጭፍ፤ ሰብዓዊ መብታቸውን ገፎ በአረመኔነት ሲያስርና ሲገርፍ፤ ከዚህም አልፎ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ሲገደሉ፤ ሴቶች ሲደፈሩና እንደውሻ ሲሳደዱ አንድም ነገር እንዳልተደረገ በማስተባበልና በኢትዮጵያም ውስጥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ሞልቶ ተትረፍርፏል እያለ ለንደን ላይ ተቀምጦ የሚወሸክተው ሆድ አደሩ አምባሳደር ብርሃኑ ከበደ ለኢትዮጵያውያን ያዘነ መስሎ ከጳጳሳቱ ጎን በክብር ተቀምጦ ታዩታላችሁ።

2ኛ) አቡነ ገብረኤልና አቡነ ቀውጦዎስ በለንደን የሚገኙ በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወኪሎችና ካድሬዎችች የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናትን በማስተባበር በስደት ሃገር የመሠረትናትን ቤተ ከርስቲያናችንን ለወያኔ አሳልፈን አንሰጥም በማለት በመታገል ላይ የሚገኙትን የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን አባላት ለማጥቃት የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ ከ02/05/15-እስከ 05/05/15 የሚዘልቅ የፈንድ ሬዚን መርሃ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

london-church4-628x319

3ኛ) እነዚሁ ሁለት ጳጳሳት ከዚህ ሁሉ በማለፍ የክርስቶስን መስቀል ተሸክመው የክርስቶስ መንገድ ከሆነው የሃይማኖቱ ሕግ የሰላም፤ የፍቅር፤ የእርቅና የይቅር ባይነት መንገድ ጨርሰው በመውጣት ውግዘትን ለፖለቲካ መሣሪያነት ለመጠቀም በመጣር ላይ ይገኛሉ።

ስለ ውግዘት ከተነሳ እነሱ ራሳቸው በስደት ላይ በሚገኘው ሕጋዊው ሲኖዶስና ቀደምት አባቶች እጅግ በጠነከረና በከረረ ውግዘት መወገዛቸውን ሁሉ ክርስቲያን የሚያውቀው ጉዳይ ነው። አሁን ላይ ግን ራሳቸው እንዳልተወገዙና እነሱም መልሰው እንዳላወገዙ ሁሉ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አገዛዝ ተጽዕኖን አንቀበልም ያሉ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላትን እኛ የምንለውን ካልተከተላችሁና በወያኔ ጫና ሥር ካልዋላችሁ እናወግዛችኋለን በማለት ውግዘትን የጎሰኝነት ፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በመጣር ላይ ይገኛሉ። ይህ እግዚኦ የሚያሰኝ ነገር አይደለም?

ይህ ሁሉ ግርግር እውነትን ከቦታዋ ባያነቃንቃትም ሆኖም ግን ጳጳሳቱ በዚህ ክርስቲያናዊ ያልሆነ ድርጊታቸው ተዋርደውና ተንቋሸው ሃይማኖታችንም ሆነ ቤተ ክርስቲያናችን መሣለቂያ ከምትሆን የማይሳነው እግዚአብሔር ልቦና ሰጥቶአቸው ከዚህ ተግባራቸው ይታቀቡ ዘንድ ልንጸልይላቸው ይገባል።

ወስብሓት ለእግዚአብሔር!!
ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት።