ከህወሀት ሰማይ ስር የሀብታሙ አያሌው ድንቅ መፅሀፍ በድጋሚ ታትሞ ለገበያ ቀርቧል።

0

 

 

ተንበርክኮ ፅፎ ነው ሌላ እዳ ‹‹እነሆ›› ያለን፡፡
************************************************
ሀብታሙ ይህን መፅሀፍ ሲፅፍ ፖለቲካ መርገማችን ያመጣበትን ቁስል ተሸክሞ ነው፡፡እንደ ብሆር የሚዘለው ጎበዝ መቀመጥ ፈተና ሆኖበት በአንድ እጁ ‹‹ተቀምጦ›› እጁ ሲዝል ተንበርክኮ ፅፎ ነው ሌላ እዳ ‹‹እነሆ›› ያለን፡፡ በበኩሌ ይህ መፅሀፍ እዳ ሆኖ ይሰማኛል፡፡መታሰርና መፈታት በአምባገነን መንግስት ምርኮ ስር ላለ ህዝብ እንደጥላ የሚከተል ልማዱ፤የንቁ ዜግነቱ ማኅተም ቢሆንም ፤መቀመጥ ሳይችሉ መፃፍን መከወን ግን ለአንባቢው ከጉተናም የከበደ ሽክም ነው ፡፡ሀብታሙ እንዲህ ሆኖ ፅፎ ለማስነበብ መትጋቱ አገር ሰላም ብሎ የኑሮ ሚዳቆውን ለሚያሳድድ አብዛኛው ዜጋ ራስን የመታዘቢያ ፌርማታ የፈጥራል፡፡
መስከረም አበራ ፀሀፊና አክቲቪስት
ከመፅሀፉ የተቀነጨበ

ከህወሀት ሰማይ ስር ያለችውን ኢትዮጵያ በማራኪ አቀራረብ ያሳየ፣ ከህወሀት ወጣት አመራርነት እስከ አንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት፣ ከቃሊቲ እስከ ቂሊንጦ፣ ከተራ የቃላት ስድብ እስከ አሰቃቂ ድብደባና ስቃይ…. በአጠቃላይ የህወሀታውያንን ስውር ገበና በአጉሊ መነፅር የሚያሳየውን ይህን ድንቅ መፅሀፍ ዛሬውኑ በእጅዎ ያስገቡ።

 

Share.

About Author

Comments are closed.