ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ በዋስትናቸው ላይ ላቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ለብይን ተቀጠሩ/2009

0

እዮኤል ፍስሀ

-የአቃቤ ሕግ ምስክር ሊቀርብ አልቻለም
———————————————-
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ሰኔ 23/2009 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀረቡ።

ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመተላለፍ ተግባር ላይ የስር ፍ/ቤት ዋስትና መብታቸውን ባለማስከበሩ ለከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታቸውን አቅርበው ስለነበር ነው፤ ዛሬ ሰኔ 23/2009 ዓ .ም ፍ/ቤት የቀረቡት። በጠበቃቸው አቶ ሽብሩ በለጠ፣ በኩል ለከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታቸውን ያቅረቡ ሲሆን፣ በችሎቱ አቃቤ ሕግ ባለመገኘቱ ጠበቃቸው ያቀረቡት መከራከሪያ ሃሳብ ላይ በፅህፈት ቤት መልስ እንዲሰጥ ከፍ/ቤቱ ውሳኔ ተላልፏል። የቦሌ ክ/ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታውን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 30/2009 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል። በተያያዘ ዜና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ትላንት ሰኔ 22/2009 ዓ.ም በቦሌ ክ/ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ የአቃቤ ሕግ ምስክር ሊቀርብ ባለመቻሉ የተነሳ ፍ/ቤቱ የአቃቤ ሕግን ምስክር ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ለሐምሌ 10/2009 ዓ.ም ሰጥቷል።

Share.

About Author

Comments are closed.