ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና መብት ተፈቀደ//2009

0

 

————————————————————————–

እዮኤል ፍስሀ

የቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና ጉዳይ ላይ ብይን ሰጠ፡፡

-እያንዳንዳቸው የ50ሺህ ብር ዋስትና እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት እና ክስ የቀረበባቸው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር አቶ ዳንኤል ሺበሺ ዛሬ ሐምሌ 10/2009 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ላይ ብይን አግኝተዋል፡፡ ፍ/ቤቱ እያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ዋስትና አቅርበው በዋስ እንዲወጡ ብይን ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል የቀረበባቸው ክስ በዝግ ችሎት እንዲታይ በተጨማሪነትም የፍርዱ ሂደቱ እስኪያልቅ ከሀገር እንዳይወጡ፣ ማረሚያ ቤቱም የፎቶ መራጃቸውን ለብሔራዊ ደኅንነት እንዲልክ ውሳኔ
ተላልፏል፡፡

ኤልያስም ሆነ ዳንኤል የቀረበባቸው ክስ በዝግ ችሎት ሊታይ አይገባም ብለው አቤቱታ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡ ፍ/ቤቱ ይህን አቤቱታ ሳይቀበለው ቀርቶ ክሳቸው በዝግ እንዲታይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በአሁኑ ሰአትም በቦሌ ክፍለከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ክሳቸው በዝግ እየታየ ይገኛል፡፡

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩም ሆነ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከሕዳር 08/2009 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Share.

About Author

Comments are closed.