የ ኢንጂኔር ስመኘው በቀለን ሞት ተከትሎ ታላቅ የህዝብ ቁጣ መቀስቀሱና ግድቡ ላይም ህዝቡ ያፈሰሰው ገንዘብ

0
የሃገራችን ህዝብ ሆይ እንኩዋን ደስ አለህ !!

የ ኢንጂኔር ስመኘው በቀለን ሞት ተከትሎ ታላቅ የህዝብ ቁጣ መቀስቀሱና ግድቡ ላይም ህዝቡ ያፈሰሰው ገንዘብ
መንግስት በ ገለልተኛ አካል እንዲጣራ እንዲያደርግ ግፊት ማድረግ መጀመሩን ተከትሎ

የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እራሱን ከፕሮጀክቱ ስራ ማግለሉን ማስታወቁ አሁን ተሰምቱዋል

የብረታ ብረት ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከአሁን በኋላ የህዳሴ ግድብ #የኤሌክትሮሜካኒካል ስራ ለቻይናው CGGC ካምፓኒ እንዲሰራለት አሳልፎ መስጠቱ ተሰምቱዋል ፡፡

መላው የሃገራችን ህዝብ እዚህ ግድብ ላይ ያፈሰሰውን ገንዘብ የሚያጣራ ገለልተኛ አካል መንግስት እንዲሾም ግፊቱን ማድረግ መቀጠሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን

እራስን በማራቅ ከተጠያቂነት ማምለጥም አይቻልም

ይህ የህዝብ ጫና ተጠናክሮ በማስቀጠል መሶቦ እና ደርባ
ሲሚንቶ ከዚ ፐሮጀክት እራሳቸውን እንዲያገሉም ምርመራም እንዲደረግባቸው ጥሪ እናደርጋለን

ለግድቡ መዘግየት ምክንያት የሆኑ አካላትና የደሃውን ህዝብ ገንዘብ ተደራጅተው የዘረፉ አካላት ባስቸኩዋይ ለ ፍርድ ይቅረቡ

ድል ለዲሞክራሲ

 

Share.

About Author

Comments are closed.