ከጅጅጋ ሸሽተው የመጡ ሰዎች እየደረሰ ያለውን በደል እያለቀሱ ገለፁ

0

ቆይ ግን የኤትዮጵያ መንግስት ለምድነው ዝም የሚለው ይሔ ሁሉ ሕዝብ ሲሞት ይሔ ሁሉ ቤተ መቅደስ ሲቃጠል ለምድው ዝምታው ምኑነው መደመር መደመር ይሔ ነው መደመር ሕዝብ እያለቀ ምድነው ዝምታ በዛ እግዚኦ ማረነ ክርስቶስ በእውነት በጣም ያማል

በጂጂጋ ግድያው ቀጥሏል፣ ኢላማ ተደርገው ግድያ እየተፈጸመባቸው ያሉት የክልሉ ተወላጅ ያልሆኑት እና በተለይም አማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ነው። እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ30 እስከ 60 የሚሆኑ ዜጎች ተገድለዋል።

ግድያው ዛሬም ቀጥሎ በቤተክርስቲያን ተሸሽገው የነበሩ ዜጎች ወጥተው ተቃውሞ በማሰማታቸው የአብዲ ኢሌ ሚሊሻዎች 3 ሰዎችን ገድለዋል፣ በርካታ ሰዎችም መቁሰላቸው ነው የሚነገረው።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ የአማራ ብሄር ተልወላጆች እና አማርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያ (ባሌ ጎባ) አሁን ደግሞ በሱማሌ ክልል በማንነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈጸመባቸው ነው።

ባለፉት 27 ዓመታት ህወሃት/ወያኔ በአማራው ብሄር ላይ ሲዘራ የነበረው ጥላቻ እንዳለ ሆኖ ዛሬም በኦጋዴን እየተካሄ ያለውን ጭፍጨፋ በመደገፍ እና በማበረታታ ላይ ይገኛል።

ይህ በዚህ እንዳለ በጅጅጋ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

//ዲያቆን ዳንኤል ክብረት//
እውነታውን ሁሉም እንዲያውቅ ሼር ያድርጉ..
…..
ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡ ክርስትናን መግደል የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡ ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች መቃጠል የሚያበቃለት ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት ነበር፡፡ ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡ ክርስትና እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን አይደርሱበትም፡፡ ንብረታችንን ይወስዱ ይሆናል፣ እምነታችንን ግን አያገኙትም፤ እኛን ይገድሉ ይሆናል፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ ናት፡፡ ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ
በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ እናውቃለን፡፡ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› ተብለናልና ተዘጋጅተን
ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረዪስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን
በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን በእርጋታ የሚሠራውን ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር
ያውካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡
…………..
እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡
ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡
….
ሁል ግዜ አስተማሪ ነገሮችን ለመከታተል ፔጁን like and follow ያድርጉ

Share.

About Author

Comments are closed.