በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ በወያኔ መንግስት ለተገደሉ ንፁሀን መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ተካሄደ

0

በወያኔ መንግስት ለተገደሉ ንፁሀን መታሰቢያ የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ተካሄደ
በህወሀት መራሹ የወያኔ መንግስት በተለያዩ ቦታዎች ለተገደሉ ንፁሀን ዜጎች መታሰቢያ እንዲሆን እና ህወሀታውያን በአማራ ልጆች ላይ የሚያደርሱትን በደል ለምእራባውያኑ ለማሳወቅ በማሰብ በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ባሳለፍነው ቅዳሜ የሻማ ማብራት መርሀ ግብር ተካሄደ። ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የዳግማዊ መዓህድ ድርጅት ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የአማራ ማህበራት አመራሮች እና አባላት በስፍራው ተገኝተዋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ዶ/ር አፈወርቅ ተሾመ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምነውን የአማራ ተወላጅ በተለያየ ጊዜ የሚያደርሰውን በደል ለማስቆም የአማራው ጠንክሮ መደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። በመቀጠልም የአማራ ማህበር በጀርመን ሊቀ መንበር አቶ ተፈሪ በግፍ የተገደሉት የአማራ ልጆች ደማቸው በከንቱ ፈሶ አይቀርም በእነሱ ሰማእትነት የድል ችቦ እንደሚለኮስ ገልፀዋል። ፕሮግራሙ ወያኔ በአማራ ልጆች ላይ የሚያደርሰውን እና ያደረሳቸውን ዘርፈ ብዙ በደሎች በአጭሩ የሚገልፅ በራሪ ወረቀት ሲታደል ቆይቶ የሰማእታቱ ፎቶዎች ስር የተቀመጡት ሻማዎች ተለኩሰው የህሊና ፀሎት ተደርጎ ተጠናቋል።

 

Share.

About Author

Comments are closed.