በሽብር ወንጀል በተከሰሱት በእነ መቶ ኣለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ውሳኔ ተሰጠ !/2009

0


[[ከ13 ተከሳሾች 7ቱ ጥፋተኛ ሲባሉ 6ቱ ጥፋተኛ አይደሉም ተብለዋል። ከ13 ተከሳሾች መካከል አቶ አጋባው ሰጠኝ እና አቶ አንጋው ተገኝ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ክስ አለባቸው ። በእነ በቀለ ገርባ የክስ መዝግብ ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 15 ተለዋዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል ]]

ለሁለት ዓመት ያህል በማዕከላዊ ፣ በቂሊንጦ እና በሸዋ ሮቢት እስር ቤቶች በተለያየ ወቅት ታስረው የነበሩ፣የሰማያዊ ፣የአንድነት እና የመኢአድ ፓርቲ አመራር እና አባላት ከብዙ እንግልት እና ስቃይ በኋል በዛሬው እለት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎትበ13 ተከሳሾች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህ ቀደም በ5ኛ ተካሽሽ አቶ ዘሪሁን በሬ ፣በ6ኛ ተካሳሽ አቶ ወርቅየ ምስጋናው እና በ7ኛ ተከሳሽ አቶ አማረ መስፍን ላይ የቀረበው ክስ፤ አቃቤ ሕግ በበቂ ሁኔታ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በተከሰሱበት ወንጀል ያስረዳ ባለመሆኑ ሦስቱ ተከሳሾች ፤ በተከሰሱበት ክስ መከላከል የማይሰፈልጋቸው በመሆኑ ፍረድ ቤቱ ከተከሰሱበት ክስ ነፃ ናችሁ ብላቸዋል፡፡

የተቀሩት 13 ተከሳሾች በእስር ቆይታቸው ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ጥሰት ይፈጸምባቸው እንደነበር በተደጋጋሚ አቤቱታቸውን ለፍርድ ቤት ያቀርብ እንደነበር የሚታወቅ ነው። አብዛኞቹ ተከሳሾች አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃቶች በተለያየ ወቅት ተፈጽሞባቸው ለሚመለከተው አካል አቤት ቢሉም መፍትሔ አለማግኝታታቸው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለፍርድ ቤት ይገልፁ እንደነበረ በጉዳዩ ዙሪያ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ሁሉም ተከሳሾች የተከሰሱት የሽብር አዋጁን በመተላለፍ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ነው።ይሁን እንጂ ተከሳሾች በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸው ክስ “ሙሉ በሙሉ ሀሰት የሆነ ፣በፖለቲካ አመለካከታቸው እና ብሔራቸውን መሰረት ያደረገ ብቻ እነሱን ለማጥቃት የተቀነባበረ ክስ ” ነው በማለት በሰው እና በሰነድ ማስረጃ የቀረበባቸውን ክስ ሲከላከሉ እና ሲቃወሙ ቆይተዋል።በዛሬው ዕለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ፣ እንዲሁም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ የተከላከሉበትን ማስረጃ ግራና ቀኙን መርምሬ ውሳኔ ሰጥቻለው በማለት ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ በንባባ አሰምቶአል ።በዚህም መሠረተ ፦
1ኛ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮነን (ጥፈተኛ አይደለም)
2ኛ በላይነህ ሲሳይ (ጥፈተኛ ነው)
3ኛ አለባቸው ማሞ (ጥፈተኛ ነው)
4ኛ አወቀ ሞኝሆዴ (ጥፈተኛ አይደለም)
8ኛ ተስፋየ ታሪኩ (ጥፈተኛ አይደለም)
9ኛ ቢሆነኝ አለነ (ጥፈተኛ ነው)
10ኛ ተፈሪ ፈንታሁን (ጥፈተኛ አይደለም)
11ኛ ፈረጀ ሙሉ (ጥፈተኛ ነው)
12ኛ አትርሳው አስቻለው (ጥፈተኛ ነው)
13ኛ እንግዳው ቃኘው (ጥፈተኛ አይደሉም)
14ኛ አንጋው ተገኘ (ጥፈተኛ ነው)
15ኛ አግባው ሰጠኝ (ጥፈተኛ አይደለም)
16ኛ አባይ ዘውዱ (ጥፈተኛ ነው) በማለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ አይደሉም ያላቸው ከዛሬ ጀምሮ ከእስር እንዲፈቱ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ፣ጥፋተኛ ናቸው ባላቸው በ7 ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ፍርድ ቤት ሰጥቷል። በእነ መቶ ኣለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ውሳኔ የሰጠው ይህ ችሎት ፣በእነ ጉርሜሳ አያኖ / በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ … አቃቤ ህግ የሽብር ክስ የቀረበባቸው የኦፌኮ አመራሮችና አባላት የእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ መርምሮ ውሳኔ ለማሰማት ለሰኔ 15 ቀን 2009 ዓ.ም የመጨረሻ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ፍርድ ቤቱ ሰጥቷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ 14ኛ ተከሳሽ አቶ አንጋው ተገኝ እና 15ኛ ተከሳሽ አቶ አግባው ሰጠኝ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ክስ አለባቸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ «ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አካባቢ የሕግ ታራሚዎች ቤተሰቦችን “መንግሥት ታራሚዎችን አቃጥሎ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ፣ አትጮሁም ወይ፣ አታለቅሱም ወይ አሁን እኛም መታገል አለብን” በማለት የሐሰት ወሬዎች በማውራት፣ ሕዝብን በመቀስቀስ እና ማነሳሳት ወንጀል» ክስ ተመስርቶብኝ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦብኝ እንደነበረ የሚታወቅ ነው። በዚሁ ክስ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቀረበው የመሰከሩ ሲሆን ፣የምስክርነት ቃላቸው ተፈጸመ ከተባለው የወንጀል ድርጊት ተመሳሳይ ያልሆነ (እርስ በርሱ የሚጋጭ) ምስክርነት የሰጡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን የቀረበብኝ ክስ እንድከላከል ብይን ሰጥቷ። በመሆኑ ሰኔ 8 ቀን 2009 ዓ.ም የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቤ ለቀረበብኝ ክስ ተከላክያለው። ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ከእኔ መከላከያ ምስክሮች ጋር አመሳክሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ለመስጠት ለሐምሌ 3/20093 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

(ይድነቃቸው ከበደ)

Share.

About Author

Comments are closed.