ለአቶ በቀለ ገርባ በአዳማ አቀባበል አድርገው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ በመቶዎች ወጣቶችን ፌደራል ፖሊስ አሰረ

0

በአዳማ ከተማ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በመውጣት ትናንት ከ እስር ለተለቀቁት አቶ በቀለ ገርባ በስታዲየም ውስጥ አቀባበል አደረጉ:: የኦህዴድ ማ ዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበበ በስታዲየሙ አቶ በቀለን ለመቀበል ለወጣው ሕዝብ ንግግር አድርገዋል::

ይህ ለአቶ በቀለ አቀባበል በሰላም ከተጠናቀቀ በኋካ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል::

በሌላ በኩልም ዛሬ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጭምሮ የተፈቱትን የሕሊና እስረኞች ለመቀበል ከወጡት ወጣቶች መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወገኖች ታስረዋል:: ከነዚህም መካከል ጋሻነህ ላቀ; ይድነቃቸው አዲስ; አዲሱ ጌታነህ; ባየልኝ ብርቁና ሲለሽ ደቻሳ ይገኙበታል:: አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ይዛችኋል እንዲሁም እስረኞችን አጅባችኋል በሚል ነው የታሰሩት::

Share.

About Author

Comments are closed.